For an Empowered and
Independent Association of
Ethiopian Legal Professionals

News and Events

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር በአራት የክልል ከተሞች ለማኅበራዊ ፍ/ቤት ዳኞች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከሁለተኛው ዙር የአውሮፓ ኅብረት ሲቪል ሶሳይቲ ፈንድ II ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ሐዋሳ፣ በኦሮሚያ ክልል አዳማ፣ በአማራ ክልል ባህር ዳር እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሦሳ የከተማ እና የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ የማኅበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች የእውቀት እና ክህሎት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ማኅበሩ ሥልጠናውን ከመስጠቱ ቀደም ብሎ በአራቱም ክልሎች የፍ/ቤቶቹን የእውቀት፣ የክህሎት፣ የተቋም ክፍተቶች የዳሰሳ ጥናት በማከናወን፣ የጥናቱ ግኝቶች ትክክለኝነት ማረጋገጫ አውደጥናት በማካሄድ እንዲሁም የየክልሎችን ዳኞች የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ማኅበሩ ለማኅበራዊ ፍ/ቤት ዳኞች ሥልጠና በሚሰጥበት ጊዜ ብዙኃኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በየክልሎቻቸው የማ/ፍ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የተሰጣቸውን ሥልጣን ግንዛቤያቸው ዝቅተኛ እንደነበር እና በአብዛኛዎቹ ማኅበራዊ ፍ/ቤቶች የማቋቋሚያ አዋጅ እንደሌላቸው ከማመልከታቸውም በላይ ሠልጣኞቹ በተለያዩ ዙሮች በተሰጡ የ3 ቀናት ሥልጠና ወደ 270 የሚጠጉ ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆኑ በተግባር የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት አጋዥ መሆኑን በመግለጽ ማኅበሩን እና የEU-CSF IIን አመስግነዋል፡፡

   DSC0606     DSC 0034 DSC0667     DSC 0210

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር በነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዙሪያ የአንድ ቀን አውደ ጥናት አካሄደ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “ክሊኒካል ሌጋል ኤዱኬሽን ፐብሊክ ኢንተርስት ፕሮጀክት” ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌደራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ አዳራሽ ውስጥ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን በሚመለከት የአንድ ቀን አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ የማኅበሩ አመራሮች፣ ከጠቅላይ ዐ/ሕግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሕግ ትምህርት ክፍል መምህራኖችና ነፃ የሕግ ድጋፍ ማዕከል አስተባባሪዎች፣ የፌደራል እና የክልል ፍ/ቤቶች ተወካዮች፣ የመንግሥት ተከላካይ ጠበቆች ቢሮ ተወካዮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሙያ ማኅበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ የሚዲያ አካላት እና ሌሎችም ተሳታፊ በሆኑበት በዚሁ ዓውደ ጥናት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፤ የቀድሞ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ታምራት ኪዳነማርያም በአወያይነት፤ እንዲሁም አቶ እንዳልካቸው ወርቁ ከጠቅላይ ዐ/ሕግ የሕግ ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት በሃሳብ ሰጭነት ተካፍለዋል፡፡

በአውደ ጥናቱ ‹‹ነፃ የሕግ ድጋፍ እና ተግዳሮቶች በፍትኃ ብሔር ጉዳዮች›› እና ‹‹የተከላካይ ጠበቆች በኢትዮጵያ፡ ክፍተቶችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚሉ ርዕሶች ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች በአቶ ጌትነት ምትኩና በአቶ አበራ ኃ/ማርያም እንደቅደምተከተላቸው ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በተለያዩ አካላት የሚሰጡ መሆናቸውና ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚስተዋሉባቸው መሆኑን፤ በተለይም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የሚለዩበት ወጥ የሆነ መስፈርት አለመኖሩ፣ የአገልግሎት ሰጪ አካላትም በቅንጅት አለመሥራታቸው፣ የአገልግሎት ጥራቱ እምብዛም መሆኑ፣ የአገልግሎት አሰጣጡ በለጋሾች የገንዘብ ድጋፍ መኖር አለመኖር ላይ የተንጠለጠ እና ቀጣይነቱ ሁልጊዜም አጠራጣሪ መሆኑ፣ የ50 ሰዓት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ወሰኑ ምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ አለመታወቁ እንዲሁም የተከላካይ ጠበቆች ቢሮ እራሱን ችሎ አለመቋቋሙ እራሱን የቻለ ተቋማዊ አደረጃጀትና መዋቅር የሌለው መሆኑና ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Register to read more...

ELA is celebrating its 50th golden jublee

Ethiopian Lawyers Association is celebrating its golden Jubilee on the current Ethiopian calendar. The Association before getting its professional association status was first established as an advocates welfare association in 1957 .Then was changed into a professional association in 1958 through registration at the then ministry of Inland affairs Yehager Gezat Minister by the name of Ethiopian Bar Association. Immediately after the 1967 revolution the Association's Amharic name was changed to Ye Ethiopia yehig balemyawoch Mahiber which literally means the Ethiopian Lawyers Association But then in 1998 the general assembly of the Association decided to restore the original Amharic name and continued functioning as a professional association. Again in 2002 The Association reregistered as an Ethiopian society in accordance with the charities and societies proclamation no. 621/2001 as Ethiopian Lawyers Association or yethiopia yehege balmuyawoch mahiber the objectives and the activities remaining the same.

During the past 50 years the Association has been functioning as the main professional association for the legal profession and has been contributing its own inputs to the development of the profession as well as the legal system as a whole.

The celebration will take place on the month of July by holding different programs among which the main ones will be a two day conference which will involve national and international legal professionals and a moot court competition.

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር

      I. ስለማኅበሩ አጭር መግለጫ

  በ1952 ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕጉ ከወጣና የዘመናዊ ሕግ ወደ ኢትዮጵያ መግባትን ተከትሎ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተቋቋመ፡፡ ከዚያም በመቀጠል በ1957 ዓ.ም. አሁን የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ተብሎ የሚታወቀው ተቋም ቀዳሚ የነበረው የጠበቆች ማኅበር በመረዳጃ ዕድር መልክ ተመሠረተ፡፡ ማኅበሩ መጀመሪያ ሲመሠረት ዓላማው በጠበቆች መካከል መልካም ሙያዊ ግንኙነት መፍጠር እና በማኅበራዊ ኑሮ መደጋገፍ ነበር፡፡ ማኅበሩ በተመሠረተ በዓመቱ “የጠበቆች ማኅበር” በሚል ስያሜ በአገር አስተዳደር ሚኒስቴር ተመዝግቦ ወደ ሙያ ማኅበርነት ተሸጋገረ፡፡ የ1967 ዓ.ም. አብዮት ሲፈነዳ ማኅበሩ ቀደም ሲል በአማርኛ ይጠራበት የነበረውን “የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር” የሚለውን ስያሜ በመለወጥ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር በሚል መልክ እንደገና ተዋቀረ፡፡ “Ethiopian Bar Association” የሚለውን የእንግሊዝኛ ስያሜ ግን ይዞ ቀጥሏል፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ “የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር” የሚለውን ስያሜ መልሶ ይዞ የነበረ ሲሆን፣ በ2001 ዓ.ም. የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ አዋጅ ከወጣ በኋላ ደግሞ በአማርኛ “የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር” በእንግሊዝኛ “The Ethiopian Lawyers’ Association” የሚለውን ስያሜ ይዞ ይገኛል፡፡

     ሀ/ በልዩ ልዩ የሕግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አባላት፣ የሕግ ባለሙያዎች እና ሌሎች ተሳታፊዎች ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ ትምህርታዊ ውይይቶችን ማዘጋጀትና ሥልጠናዎችን መስጠት

    ለ/ እስከ 2001 ዓ.ም. ባሉት አመታት ጠበቆችን በመወከል በፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ በጠበቆች የዲሲፒሊን ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት መሳተፍ፣

    ሐ/ የጠበቆችን መብት ለማስከበር መጣር

    መ/ ዐቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ማኅበሩ በራሱ ወይም በአባሎቹ አማካኝነት የነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠት፣

    ሠ/ አልፎ አልፎ በመንግሥት ወይም በፓርላማ ሲጠየቅ በረቂቅ ሕጐች ላይ ሙያዊ አስተያየት መስጠት፣

    ረ/ በልዩ ልዩ ወቅታዊ፣ አገራዊ እና የሕግ ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸውን (ሴክተር) የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ሌሎች አካላትን በማሳተፍ የሕግ ግንዛቤ መፍጠር፤ ሕጋዊነት የሚጐላቸው አሠራሮች እንዲወገዱ፣ አዳዲስ ሕጐች እንዲወጡ እንዲሁም መሻሻል የሚገባቸው ሕጐች እና አሠራሮች እንዲሻሻሉ አስተያየት መስጠት

    ሰ/ ከ1998 ዓ.ም. ወዲህ ደረጃውን የጠበቀ የኢትዮጵያ ጠበቆች የሕግ መጽሔትን በማቋቋም በልዩ ልዩ የሕግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን ማሳተም፣

    ሸ/ የመላው አፍሪካ የጠበቆች ኅብረት (Pan African Lawyers Union) እንዲቋቋምና ዋና መቀመጫው አዲስ አበባ እንዲሆን ግፊት አድርጐ ማስወሰን እና የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት በቋሚነት የመላው አፍሪካ የጠበቆች ኅብረት ዋና ፀሐፊ ሆኖ እንዲያገለግል ማስወሰን፣   ይገኙበታል፡፡

Register to read more...

Support Ethiopian CSO

 CSF II Support Ethiopian CSO

 

 

PUBLICATION

 

 

 

 

 

 

EVENTS

November 2023
S M T W T F S
29 30 31 1 2 3 4
5 6 7 8 9 10 11
12 13 14 15 16 17 18
19 20 21 22 23 24 25
26 27 28 29 30 1 2